የተጣሩ መረጃዎች

ሀሰት፡ ምስሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ አያሳይም

በየካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የትዊተር አካውንት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ ያሳያል በማለት አንድ ምስልን አያይዞ አጋርቶ ነበር። 

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የትዊተር ፖስት ከ2ሺህ በላይ እይታን ማግኘት የቻለ ሲሆን ከ50 ጊዜ በላይ ደግሞ መጋራት ችሏል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ በአሁኑን ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ድርቅ እንደማያሳይ በማረጋገጥ የትዊተር ፖስቱን ሀሰት ብሎታል።     

የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኦሮሚያ እና የሶማልያ ክልል አካባቢዎች ላይ ከባድ ድርቅ መከሰቱን ያሳያሉ።

ይህ ድርቅ በእነዚህ አካባቢዎች ለአምስት ተከታታይ አመታት ተከስቷል። ይሁን እንጂ በነዚህ አካባቢዎች ከተከሰቱት ድርቆች መካከል በቦረና የተከሰትው ድርቅ ከባዱ ነው።

በምስራቃዊ እና ደቡባዊ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለይም የቦረና አካባቢ ባለፉት አመታቶች ከባድ በሆነ ድርቅ የተጎዳ አካባቢ ነው። ከዚህ ድርቅ ጋር በተያያዘ በባለፈው አመት በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ፤ ሴቶች እና አረጋውያን በምግብ እጥረት እና በድርቁ ምክንያት የቀንድ ከብቶቻቸውን በማጣታቸው ምክንያት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው ነበር። 

በአሁኑ ሰዓት በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከአየር ንብረት መለዋወጥ እንዲሁም እነዚህ አካባቢዎች  ዝናብ በማጣታቸው ምክንያት የተከሰተ ነው። 

ይህ ድርቅ ወደ 800ሺህ የሚጠጉ የዞኑ ነዋሪዎችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል።          

በኢትዮጵያ በምስራቁ ክፍል እና እንደ ቦረና ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ማለት በሚቻል መልኩ በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ሲሆኑ ህልውናቸው በቀንድ ክብቶቻቸው ላይ የተመሰረተ ነው። 

ይህ ለአምስት ተከታታይ አመታት የጠፋው ዝናብ የቦረና እና አካባቢው ነዋሪዎችን ህይወት አበላሽቷል። 

በዚህ መረጃ ላይ ተመስርቶ ይህ የትዊተር አካውንት የሞቱ የቀንድ ከብቶችን ምስል በማያያዝ በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተውን ድርቅ ያሳያል በማለት አጋርቶት ነበር።     

ይሁን እንጂ ምስሉ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቦረና እና አካባቢው ያለውን ድርቅ አያሳይም።

ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ ነበር።

በወቅቱ የተጋራው ይህ የፌስቡክ ፖስት በኦሮሚያ የባሌ እና ቦረና አካባቢዎች በድርቅ መጠቃታቸውን እንደሚያሳይ ከሚገልፅ ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ ነበር። 
ስለዚህ ሀቅቼክ በአሁኑ ወቅት በቦረና ዞን አስከፊ ድርቅ ቢኖርም ነገር ግን ይህ የትዊተር ፖስት የቆየ ምስልን በመጠቀሙ ምክንያት ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ምስሉ በአቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

በጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የትዊተር አካውንት ህገወጥ የጦር መሳርያዎች እና ጥይቶች በባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የፓትርያርኩ ፅ/ቤት አመራር በሆኑት በአቶ አቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ ተገኝተዋል በማለት ሶስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር።

ይህ የትዊተር ፖስት በፖሊስ ፍተሻ ከአቡነ አብርሃም የመኖርያ ቤት ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ መሳርያዎች ከ235 ጥይት ጋር ተገኝቷል የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አጋርቶ ነበር።  

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የትዊተር ፖስት ወደ አንድ መቶ ያህል ጊዜ መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተመልክተውታል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ተመልክቶ መረጃውን እንደማይደግፍ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል። 

በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን ሾመዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ እና ሁለት ሌሎች ጳጳሳት አንድ ላይ በመሆን ወደ 26 የሚጠጉ ኤጲስ-ቆጶሳትን በተለያዩ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሾመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአቡነ ሳዊሮስ አማካኝነት ወደ 70 የሚጠጉ ጳጳሳት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ደብሮች ላይ ተመድበው ነበር።

ከዚህ ሁኔታ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን በመጥራት ከቤተክርስትያኗ እውቅና ውጭ የተሾሙትን ጳጳሶች እና በሹመቱ ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አውግዛለች።

ከዚህም በተጨማሪ የቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እነ አቡነ ሳዊሮስን እና ሌሎች ጳጳሳትን የቤተክርስትያኗን ቀኖና በመተላለፋቸው ምክንያት ከአባልነት አስወግዳቸዋለች።    

ከጥቂት ቀናት በኋላ ከቤትክርስትያኗ ተለይተው የወጡት ሊቀጳጳሳትም በበኩላቸው ወደ 12 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳትን በማውገዝ ከአባልነትም ማገዳቸውን አስታውቀው ነበር። 

የባህርዳር ሀገረስብከት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስትያን ሊቀጳጳስ የሆኑት አቶ አቡነ አብርሃም ከቤትክርስትያኗ በተለዩት አዳዲሶቹ ሊቀጳጳሳት ከተገለሉት መካከል ናቸው።

በጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም የተጋራው ይህ የትዊተር ፖስት ህገወጥ የጦር መሳርያዎች እና ጥይቶች በባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የፓትርያርኩ ፅ/ቤት አመራር በሆኑት በአቶ አቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ ተገኝተዋል በማለት ሶስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ይህ የትዊተር ፖስት በአቡነ አብርሃም የመኖርያ ቤት ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ መሳርያዎች ከ235 ጥይት ጋር ተገኝቷል የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አጋርቶ ነበር።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ በዚህ የትዊተር አካውንት የተጋራውን መረጃ ተመልክቶ የተጋሩት ምስሎች የቆዩ እና መረጃውን የማይደግፉ እንደሆኑ አረጋግጧል። 

የመጀመርያው ምስል በአዲስ አበባ ቅንጡ የሆኑ ሆቴሎችን በሚያስተዋውቅ አንድ ድረ-ገፅ ላይ የተወሰደ ሲሆን እንደ ድረገፁ ከሆነ ምስሉ በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በሚገኝ እና ሸገር ሮያል የተሰኘ ሆቴል የውስጥ ክፍሎችን እንደሚያሳይ ተገልጿል።    

ሁለተኛው ምስል በመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአንድ የዜና ድረ-ገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን ከተጋራው ምስል ጋር ህንድ ከሩሲያ ጋር የ770,000 ክላሽንኮቭ መሳርያዎችን ለመግዛት የግዥ ስምምነት መፈፀሟን በሚያሳይ ፅሁፍ ስር አገኝቶታል።  

ሶስተኛው ምስል ደግሞ የአቡነ አብርሃም መሆኑ ይታወቃል። 

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ የትዊተር አካውንቱን ፖስት መርምሮ ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት ፡ ምስሉ በጅማ ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ግለሰብ አመራር ቤት ውስጥ የተገኘን የጦር መሳርያ አያሳይም

በጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከ290ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ “በጅማ ከተማ በአንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያ።” በማለት ሶስት ምስሎችን በማያያዝ አጋርቶ ነበር። 


የመጀመርያው ምስል የተለያዩ ጠመንጃዎችን የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ምስል የጥይት እና የጦር መሳርያ ምስሎችን ያሳያል። ሶስተኛው ምስል ደግሞ የጦር መሳርያ የተገኘበትን ግለሰብ ምስል ያሳያል በማለት አጋርቶት ነበር። 

ከዚህም በተጨማሪ  ይህ የፌስቡክ ፖስት በምስሉ ላይ የተመለከተው ግለሰብ “በጅማ የማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ሰብሳቢ እና የደብተራ መድሃንያለም ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ነው።” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አብሮ አያይዟል።

ይህ የፌስቡክ ፖስት በብዙ ስዎች ዘንድ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን ከ400 በላይ ግብረ መልሶችን ማግኘት ችሏል። 

ይሁን እንጂ ምስሎቹ የቆዩ ሲሆኑ በፌስቡክ ገፁ የቀረበውን መረጃ እንደማይደግፉ ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ መረጃውን ሀሰት ብሎታል።    

በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን ሾመዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ እና ሁለት ሌሎች ጳጳሳት አንድ ላይ በመሆን ወደ 26 የሚጠጉ ኤጲስ-ቆጶሳትን በተለያዩ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሾመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአቡነ ሳዊሮስ አማካኝነት ወደ 70 የሚጠጉ ጳጳሳት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ደብሮች ላይ ተመድበው ነበር።

ከዚህ ሁኔታ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን በመጥራት ከቤተክርስትያኗ እውቅና ውጭ የተሾሙትን ጳጳሶች እና በሹመቱ ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አውግዛለች።

ከዚህም በተጨማሪ የቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እነ አቡነ ሳዊሮስን እና ሌሎች ጳጳሳትን የቤተክርስትያኗን ቀኖና በመተላለፋቸው ምክንያት ከአባልነት አስወግዳቸዋለች።    

ከጥቂት ቀናት በኋላ ከቤትክርስትያኗ ተለይተው የወጡት ሊቀጳጳሳትም በበኩላቸው ወደ 12 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳትን በማውገዝ ከአባልነትም ማገዳቸውን አስታውቀው ነበር። 

በዚህ መረጃ ላይ በመመስረት በጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የፌስቡክ ፖስት ሶስት ምስሎችን በማያያዝ “በጅማ የማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ሰብሳቢ እና የደብተራ መድሃንያለም ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር በሆኑ ግለሰብ መኖርያ ቤት ውስጥ የጦር መሳርያ ተገኘ” በማለት አጋርቶ ነበር። 

የመጀመርያዎቹ ሁለት ምስሎች እንደ ማስረጃነት የተለያዩ የጠመንጃ እና የጥይት ምስሎችን የሚያሳዩ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የግለሰቡን ምስል ያሳያል። 

ጠመንጃዎች የሚታዩበት የመጀመርያው ምስል በጥቅምት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በቢቢሲ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ የጦር መሳርያ መያዙን በሚገልፅ ፅሁፍ ስር ተጋርቶ ተገኝቷል።       

ሊንክ

ሁለተኛው ምስል ደግሞ በመስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የሀገር ውስጥ የዜና ሚድያ ላይ ከተጋራ ፅሁፍ ላይ የተወሰደ ነው። በዜናው ላይም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ የጦር መሳርያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እደሚያሳይ ይገልፃል።   

ሊንክ
በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ የፌስቡክ ፖስቱን ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ምስሉ በሻሸመኔ የኦርቶዶክስ ቤትክርስትያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

ከ39ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ “ይህ በሻሸመኔ ቤተ እምነት ቅጥር ግቢ ውስጥ በፍተሻ የተገኘ ነው።” የሚል ፅሁፍን በማያያዝ አንድ ምስል አጋርቶ ነበር። 

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ13 ጊዜ በላይ መጋራት ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ የቆየ እና ከዚህ መረጃ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አረጋግጧል። 


ስለዚህም ሀቅቼክ ይህን የፌስቡክ ፖስት ሀሰት ብሎታል።   

በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን ሾመዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ እና ሁለት ሌሎች ጳጳሳት አንድ ላይ በመሆን ወደ 26 የሚጠጉ ኤጲስ-ቆጶሳትን በተለያዩ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሾመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአቡነ ሳዊሮስ አማካኝነት ወደ 70 የሚጠጉ ጳጳሳት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ደብሮች ላይ ተመድበው ነበር።

ከዚህ ሁኔታ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን በመጥራት ከቤተክርስትያኗ እውቅና ውጭ የተሾሙትን ጳጳሶች እና በሹመቱ ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አውግዛለች።

ከዚህም በተጨማሪ የቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እነ አቡነ ሳዊሮስን እና ሌሎች ጳጳሳትን የቤተክርስትያኗን ቀኖና በመተላለፋቸው ምክንያት ከአባልነት አስወግዳቸዋለች።    

ከጥቂት ቀናት በኋላ ከቤትክርስትያኗ ተለይተው የወጡት ሊቀጳጳሳትም በበኩላቸው ወደ 12 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳትን በማውገዝ ከአባልነትም ማገዳቸውን አስታውቀው ነበር። 

ከቤትክርስትያኗ ተለይተው የወጡት ሊቀጳጳሳት መሪ የሆኑት አቡነ ሳዊሮስ አቡን ጳውሎስን የምዕራብ አርሲ ሀገረስብከት በሻሸመኔ ከተማ አመራር አድርገው መሾማቸው ይታወቃል። አዲስ የተሾሙት ጳጳስ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ለመግባት መጓዛቸውን ተከትሎ በከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። 

እንደተለያዩ የዜና ሪፖርቶች ከሆነ በከተማዋ በተከሰተው ግጭት ወደ ሶስት የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።  

ይህ የፌስቡክ ፖስትም በዚህ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተጋራ ነው።

ሀቅቼክ መረጃውን ይደግፋሉ የተባሉትን ምስሎች ለማጣራት በደረገው ጥረት ምስሎቹ የቆዩ እና ከሁለት አመት በፊት ተጋርተው የነበሩ መሆናቸውን አረጋግጧል። 

ምስሉ ለመጀመርያ ጊዜ በመጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፌስቡክ ገፅ ላይ “የፌደራል ፖሊስ በሲዳማ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳርያ በቁጥጥር ስር ውሏል።” በሚል መግለጫ ተጋርቶ ነበር። 

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ የፌስቡክ ፖስቱን ሀሰት ብሎታል። 

ሀሰት፡ ምስሉ በቅርቡ በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ የተከሰተውን ግጭት አያሳይም

ከሰሞኑ በአጣዬ እና አካባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ የሚቃጠሉ ቤቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚድያው ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።

በጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ከሰሞኑ በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ በተከሰተው ግጭት የሚቃጠሉ ቤቶች የሚያሳይ ምስል በሚል መግለጫ ስር አንድ ምስል አጋርቶ ነበር።


ይህ ምስል ከሌሎች ሁለት ምስሎች ጋር በመሆን ሲጋራ የቆየ ሲሆን ከሁለት ሰዓታት በኋላ በአጣዬ ከተማ ከተከሰተው ግጭት ጋር በማያያዝ ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ባለው አንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቷል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ ለመጀመርያ ጊዜ ከሶስት አመት በፊት በአንደ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረ እንደሆነ እና አሁን በአጣዬ እና አካባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር እንደማይገናኝ አረጋግጦ የፌስቡክ ፖስቱን ሀሰት ብሎታል።

ሊንክ

ሊንክ

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ልዩ ዞኖች እንዲሁም አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተከታታይ የሆነ ግጭት እና ግድያዎች ተፈፅመዋል። በጥቅምት 2011 ዓ.ም የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ በጊዜው በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ሶስት ሰዎች እንደሞቱ ገልጿል።

ከሁለት አመታት በኋላ በ2013 ዓ.ም በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን ቦታዎች በተለይም በአጣዬ ከተማ ላይ ከባድ ግጭቶች ተከስተው ነበር።   

ግጭቱ ለሁለት ወራት ያክል ቆይቶ የነበረ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ሰዎች ሲሞቱ በግጭቱ የቆሰሉም አሉ። በዚህ ግጭት ምክንያት በመጋቢት እና ሚያዝያ 2011 ዓ.ም ላይ ከ3 መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ3000 በላይ ቤቶች በቃጠሎ ምክንያት ወድመዋል።    

አንድ አራተኛ የሚሆነው የአጣየ ከተማ ክፍል በዚህ ግጭት ምክንያት ወድሟል። ይህ ግጭት ካስከተለው ጉዳት በኋላ የአማራ ክልል መንግስት ለመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ወደ 1.5 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልገው ገልጾ ነበር።  

በሚያዝያ ወር 2012 ዓ.ም ላይ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች ላይ ግጭቶች ተከስተው የነበረ ሲሆን ይህ ግጭት ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

ከሰሞኑ በሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ልዩ ዞን በሚገኙት የአጣዬ እና የጀውሃ ከተሞች አካባቢ ግጭት መከሰቱን የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ሪፖርቶች ያሳያሉ። 

ይህ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ ምስሉ በአጣዬ ከተማ የተፈፀመ ነው በማለት በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ ሲዘዋወር ቆይቷል።


ይህ ምስል በጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ በሁለት የፌስቡክ ገፆች ላይ የተጋራ ሲሆን ሁለቱም የፌስቡክ ገፆች እያንዳንዳቸው ከ5ሺህ በላይ ተከታዮች አሏቸው።  

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ የቆየ እና ከሰሞኑ በአጣዬ እና አካባቢው ከተፈጠረው ግጭት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ችሏል።

ምስሉ ከሶስት አመት በፊት ሚያዝያ ወር 2011 ዓ.ም ላይ በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ ነበር። ከምስሉ ጋር ያለው ፅሁፍ በወቅቱ በአጣዬ ከተማ በእሳት ቃጠሎ የተጠቃ ቤተክርስትያን እንደሚያሳይ ይገልፃል። ስለዚህ ሀቅቼክ መረጃውን አጣርቶ ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ይህ ቪድዮ በወሎ በተከሰተው ግጭት የተቃጠለ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ቤቶችን አያሳይም

በጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ ከ6ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ “በአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ቤቶች እየተቃጠሉ ነው።” በማለት አንድ ቪድዮን አጋርቶ ነበር።


ከዚህ በተጨማሪም ይህ የፌስቡክ ገፅ በአካባቢው ያሉ የታጠቁ ሚሊሽያዎች የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ንብረት እየዘረፉ እና እየገደሉ ነው በማለት መረጃን አጋርቷል።  
 

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ይህ የፌስቡክ ገፅ በቪድዮው ውስጥ የተጠቀመው ምስል የቆየ እንደሆነ እና መረጃውን እንደማይደግፍ አረጋግጦ ሀሰት ብሎታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በሆኑ አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭቶች በተደጋጋሚ እየተፈጠሩ ይገኛሉ።  

እንደ አንድ አንድ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ከሆነ ከሰሞኑ በነዚህ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተዋል።  

በጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች በአማራ ክልል ታጣቂዎች አማካኝነት የተቀናጀ ጥቃት በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ተፈፅሟል በማለት ገልጿል።   

ከዚህ በተጨማሪም በመግለጫው ላይ የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች እና የአካባቢው ሚሊሽያዎች በጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ፤ ቤቶችን እንዳቃጠሉ እና ንብረቶችን እንደዘረፉ ገልጿል። 

ከዚህ በተጨማሪም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በግጭቱ ከ65 በላይ ንጹሀን መሞታቸውን በመግለጫው ላይ አንስቷል።  

ይህ የፌስቡክ ፖስትም የሚቃጠሉ ቤቶችን የሚያሳይ የምስል ቪድዮ ያጋራው በዚህ ሀሳብ ላይ መሰረት አድርጎ ነው።


ይሁን እንጂ ከቪድዮው ማየት እንደሚቻለው ምስሎችን ገጣጥሞ በመጠቀም የተፈጠረ ነው።     

ነገር ግን በቪድዮው ውስጥ ያለው ምስል ከዚህ በፊት በታኅሣሥ 14 ቀን  2013 ዓ.ም ከተጋራ ፅሁፍ ላይ የተወሰደ ነው።  

ሊንክከዚህ ፅሁፍ ጋር የተጋራው ምስል በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን የሚኖሩ ብዙ ንፁሃን እንደተገደሉ በሚያሳይ ሪፖርት ስር ተጋርቷል።

ሀቅቼክ በዚህ የፌስቡክ ገፅ አማካኛነት መረጃውን ለመደገፍ የተጋራው ምስል የቆየ እና ከዚህ መረጃ ጋር የማይገናኝ መሆኑ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል። 

ሀሰት፡ ምስሉ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ውስጥ የተገደሉ የአማራ ብሄር ተወላጆችን አያሳይም

በኅዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከ7 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ የአማራ ብሄር ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ላይ እየተገደሉ ነው በማለት አንድ ምስል አጋርቶ ነበር። 

ይህ የፌስቡክ ገጽ በአያያዘው ምስል ላይ “በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለ ዘር ማጥፋት” የሚል ፅሁፍ አድርጎበታል። 

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ39 ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል። 

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን መርምሮ ሀሰት ብሎታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ በተለያዩ የእርስ በርስ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ውስጥ እያለፈች ትገኛለች። በእነዚህ ጊዜያቶችም ውስጣዊ የድንበር ግጭቶች ፤ የብሄር ግጭት ፤ ሞት እና መፈናቀሎችም ተከስተዋል።

ከነዚህ ክስተቶች መሃልም በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል ተከስቶ የነበረው እና ለሁለት አመት ቆይቶ የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ይጠቀሳል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ውስጥ በተከሰተው ግጭት ምክንያት በተደጋጋሚ የተለያዩ የጅምላ ግድያዎች ፤ ሞት እና መፈናቀሎች እየተሰሙ ይገኛሉ።

በዚህም ግጭት ምክንያት ንፁሃን የአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች የዚህ ግጭት ሰለባ ሆነዋል። የዜና ሪፖርቶች በነዚህ ግጭት በተባባሰባቸው አካባቢዎች የአማራ ብሄር ተወላጆች እንደሚገደሉ እና እንደሚፈናቀሉ ያሳያሉ። 

ይህን የሰዎች ሞት እና መፈናቀልን ተከትሎ መንግስት ድርጊቱን የፈፀመው ኦነግ ሸኔ ነው ቢልም ኦነግ ሸኔ በተቃራኒው ነገሩን ሲያስተባብልና መንግስትን ሲከስ ቆይቷል።      

ይህ የፌስቡክ ፖስትም በዚህ ሀሳብ ላይ መሰረት አድርጎ የተጋራ ነው።  

ሀቅቼክ ባደረገው ማጣራት መሠረት ምስሉ የቆየ እና በሐምሌ 2012 ዓ.ም በአንድ የዜና ድረገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረ ነው። 

ምስሉ ለመጀመርያ ግዜ በአንድ የዜና ድረገፅ ላይ የተጋራ ሲሆን፤ ሁለት የሶማልያ ወታደሮች በደቡብ ምዕራብ ሶማልያ በምትገኘው እና ባይዶአ ተብላ በምትጠራው አካባቢ የ10 አመት ወንድ ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀማቸውን ተከትሎ በአደባባይ ተሰቅለው በጥይት እንደተገደሉ የሚያሳይ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።
 

ከዚህ በተጨማሪም ይህ የዜና ምንጭ ሁለቱ ወታደሮች በሶማልያ የ60ኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች በጥይት ተመተው ከመገደላቸው በፊት በከተማዋ ውስጥ ታስረው ሲዞሩ እና በህዝብ ፊት ሲታዩ እንደነበረ ዘግቧል።
ስለዚህ ሀቅቼክ ይህ የፌስቡክ ፖስት የተጠቀመውን ምስል መርምሮ ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ምስሉ በኦሮሚያ ክልል የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለ እስርን አያሳይም

በታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ ከ64 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አንድ የፌስቡክ ገፅ “ወለጋ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ብሎ የፈረጀውን  ኦነግ ሸኔን ለምን ተጋጠማችሁ ብሎ አማሮችን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማሰር ጀምሯል።” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን በማያያዝ አንድ ምስል አያይዞ አጋርቶ ነበር። 

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ የፌስቡክ ፖስቱ ከ130 በላይ ግብረ መልስ ሲያገኝ ከ30 ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል። 

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይሎች የአማራ ተወላጆችን ማሰር ጀምረዋል ተብሎ የተጋራው ምስል ትክክለኛነት አጣርቶ ሀሰት ብሎታል።

የፌደራሉ መንግስት እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው እና በሌሎች ደግሞ ኦነግ ሸኔ እየተባለ ከሚጠራው አካል ጋር ጦርነት ውስጥ እንደገባ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ቆይቷል። በሁለቱ አካላት መካከል የተከሰተው ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተስፋፋ መጥቷል። 

በዚህ ግጭት ምክንያት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በወለጋ አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።  

የፌደራሉ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጋር ተከታታይ የሆነ ግጭት እና ጦርነት ውስጥ እንደሆነ የሚያሳዩ ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል። ይህ በዋነኝነት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ አካባቢ በሁለቱ አካላቶች መካከል የተከሰተው ግጭት በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአጎራባች አካባቢዎችም ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ አለመረጋጋት ፣ የሰው ሞት እና መፈናቀልን እያመጣ ይገኛል።

የፌደራሉ መንግስት እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ለሚፈጠሩ የሰው ልጅ ሞት እና መፈናቀሎች ተጠያቂው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ብለው ሲገልፁ በተቃራኒው ደግሞ ኦነግ ሸኔ ንፁሃን ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ተጠያቂው እራሱ መንግስት ነው ሲል ሲከስ ይደመጣል።

አዲስ ስታንዳርድ የተሰኘው የሀገር ውስጥ ጋዜጣ የአይን ምስክሮች ነገሩኝ ብሎ ባጋራው መረጃ መሰረት  በህዳር ቀን 16 እና 20 2015 ዓ.ም ላይ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ የአማራ ክልል ፋኖ ታጣቂዎች ብዙ ሰው መግደላቸውን ዘግቧል።  

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን አካባቢ ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የተከሰተው ግጭትም የብዙ ንፁሀንን ህይወት ቀጥፏል።  በዚህም ግጭት የተነሳ ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ከመኖሪያ ቦታቸው እንደተፈናቀሉ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

በዚህ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተሰራጨው ይህ መረጃም በዚህ ሀሳብ ላይ ተመስርቶ ነው።

ሀቅቼክ መረጃውን ለመደገፍ የተጋራውን ምስል ለማጣራት ባደረገው ጥረት መሰረት ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋራው ሚያዝያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በቢቢሲ የኦሮምኛ ቋንቋ እትም ላይ ሲሆን በቢቢሲ ዘገባ መሰረት ምስሉ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን አብዶ አባ ጆቢር የተባለ መምህር በክልሉ ልዩ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የሚያሳይ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ ምስሉን መርምሮ ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ምስሉ በቤንሻንጉል ክልል በኦሮሚያ ልዩ ሀይሎች እና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አማካኝነት የሚቃጠል የአማራ ተወላጆችን ቤት አያሳይም

በታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ ከ20ሺህ በላይ ተከታይ ያለው አንድ የፌስቡክ ገፅ “በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዥጋ ወረዳ መንደር 42/ተንካራ ላይ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ  ከአርጆ ጉደቱ በመነሳት ወረራ የፈጸመው መንግስት መሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ሰላማዊ አማራዎችን በጅምላ በማጥቃት መኖሪያ ቤቶችን እያቃጠለ እና እየዘረፈ ነው።”  የሚል የመግለጫ ፅሁፍን በማያያዝ አንድ ምስል አጋርቶ ነበር።

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ የፌስቡክ ፖስቱ ከ190 በላይ ግብረመልስን ሲያገኝ ከ30 ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ይህ የፌስቡክ ፖስት መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀመውን ምስል አጣርቶ ሀሰት ብሎታል።

የፌደራሉ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከኦነግ ሸኔ ትጣቂዎች ጋር ተከታታይ የሆነ ግጭት እና ጦርነት ውስጥ እንደሆነ የሚያሳዩ ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል። ይህ በዋነኝነት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ አካባቢ በሁለቱ አካላቶች መካከል የተከሰተው ግጭት በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአጎራባች አካባቢዎችም ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ አለመረጋጋት ፣ የሰው ሞት እና መፈናቀል እየተፈጠረ ይገኛል።

የፌደራሉ መንግስት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ለሚፈጠሩ የሰው ልጅ ሞት እና መፈናቀል ተጠያቂው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ብለው ሲገልፁ በተቃራኒው ደግሞ ኦነግ ሸኔ ንፁሃን ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ተጠያቂው እራሱ መንግስት ነው ሲል ሲከስ ይደመጣል።

በቤንሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን እና አካባቢው ተከታታይ የሆኑ ግጭት ፣ ሞት እና መፈናቀሎች ሲከሰቱ የቆዩ ሲሆን ይህ አካባቢም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች ጋር ድንበር እና ወሰኖችን ይጋራል።

 
በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን አካባቢ ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የተከሰተው ግጭትም የብዙ ንፅሁንን ህይወት ቀጥፏል።  በዚህም ግጭት የተነሳ ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ከመኖሪያ ቦታቸው እንደተፈናቀሉ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

በዚህ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተሰራጨው ይህ መረጃም በዚህ ሀሳብ ላይ ተመስርቶ የተጋራ ነው።

የፌስቡክ ገፁ በቤንሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይሎች ከኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በመሆን የአማራ ተወላጆችን ቤት እያቃጠሉ ነው የሚለውን መረጃ ይደግፍልኛል በማለት አንድ ምስልን አያይዞ ነበር።

ይሁን እንጂ ይህ የፌስቡክ ገጽ እንደተናገረው ምስሉ ከኦሮሚያ ክልል በመጡ ታጣቂዎች አማካኝነት የሚቃጠል የአማራ ተወላጆች ቤቶችን አያሳይም።

ሀቅቼክ የምስሉን ትክክለኛነት ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉን ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ከተጋራ አንድ ፅሁፍ ውስጥ አግኝቶታል። ይህ ምስል በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ውስጥ በነበረው ግጭት ላይ የተቃጠሉ ቤቶችን እንደሚያሳይ ከሚገልፅ ፅሁፍ ጋር አብሮ ተጋርቷል።

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ ምስሉን መርምሮ ሀሰት ብሎታል።

ሀሰት፡ ምስሉ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በአዲስ አበባ ከተማ በተማሪዎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ አያሳይም

በታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ አንድ የፌስቡክ ገፅ “ወላጅ ልጆቹን ትምህርት እንዲቀስሙለት ትምህርት ቤት ይልካል ባለ ጊዜ እንዲህ ያደርጋል” የሚል ፅሁፍን በማያያዝ አንድ ምስልን አጋርቶ ነበር። 

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ400 ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል። 

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ በቅርቡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ ጋር ተነስቶ ከነበረው ግጭት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ አረጋግጦ ምስሉን ሀሰት ብሎታል።  

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልላዊ መዝሙር እና የባንዲራ መሰቀል ጋር ተያይዞ በተማሪዎች እና በፀጥታ አካላት መካከል ግጭት ተከስቶ እንደነበር የሚያሳዩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋዊ የማህበራዊ ገፁ ላይ ባሰራጨው መረጃ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የሚሰሩ የግጭት ነጋዴዎችን በጋራ በመከላከል አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል እንዳሉ ያስነበበ ሲሆን ከንቲባዋ አያይዘውም ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሰንደቅ ዓላማ ጋር በማያያዝ ግጭት ለመቀስቀስ የተሞከረው ጥረት የዚሁ አካል መሆኑንም ገልፀዋል።” 

ህዳር 29 ቀን 2015 ዓም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ግጭትን ለመቀስቀስ እና ለማባባስ ሲሰሩ ነበሩ ያላቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።  

ፖሊስ በመግለጫውም ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተማሪ እና አስተማሪዎች የኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራን ከተሰቀለበት በማውረድ ግጭትን ለማባባስ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውንም ጨምሮ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በታህሳሰ 3  ቀን 2015 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ የፀጥታ ሀይሉ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ወስጥ ግጭትን ለመቀስቀስ አስበዋል ያላቸውን 72 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።     

ከዚህ በተጨማሪም ሀቅቼክ በታህሰሳ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ ሀይሎች በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚያሳዩ ቪድዮውች ሲዘዋወሩ ተመልክቷል። 

በዚህ ሳምንት የወጡ አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የፌደራል መንግስት  በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮምያ ክልል ባንዲራ እንዲሰቀልና መዝሙር እንዲዘመር እየተደረገ ያለው ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ እንዲቆም መመሪያ መስጠቱን ያሳያሉ። 

ይህ የፌስቡክ ፖስትም በነዚህ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ የተጋራ ነው።

ሀቅቼክ የፌስቡክ ፖስቱ መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀመውን ምስል ትክክለኛነት ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉን በ2009 ዓ.ም የሂዩማን ራይትስ ዎች ድረገፅን ጨምሮ በሌሎች ድረገፆች ላይ በ2009 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው የመንግስት ተቃውሞ  ላይ በኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው አመፅ ምክንያት በኦሮሚያ የፀጥታ ሀይሎች የተያዙ ተማሪዎች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ የሚያሳይ እንደሆነ በሚያሳይ የፅሁፍ መግለጫ ስር ተጋርቶ አግኝቶታል። 

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተማሪዎች እና በፀጥታ አካላት መካከል ግጭት ተከስቶ እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች ቢኖሩም ይህ የፌስቡክ ገፅ መረጃውን ይደግፍልኛል ብሎ ያጋራው ምስል የተሳሳተ ነው።በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ ምስሉን መርምሮ ሀሰት ብሎታል።  

Exit mobile version