ስለ ሀቅቼክ
ሀቅቼክ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ላይ የሚታዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች እያጣራ ያቀርባል። ሀቅቼክ በአዲስ ዘይቤ የዜና ክፍል ውስጥ ህዳር 2013 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኢንፎርም አፍሪካ በተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሲቪል ማህበር ስር ሀሰተኛ መረጃን የመከላከል ፕሮጀክት በመሆን እየሰራ ይገኛል።
ሀቅቼክ ከሌሎች የሚድያ አውታሮች ጋር በመቀናጀት የሚድያው ምህዋር ላይ የሚስተዋሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያጣራ እንግሊዝኛን ጨምሮ በ4 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች (በአማርኛ ፤ በአፋን ኦሮሞ ፤ በትግርኛ እና በሶማሊኛ) እያጣራ ያቀርባል። ሀሰተኛ መረጃን ከማጣራት በተጨማሪም የማህበረሰቡን የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ክህሎት ለማሳደግ ይሰራል።
ሀቅቼክ በየሳምንቱ የሀሰተኛ መረጃ ዳሰሳ እና በየወሩ የዳሰሳ ትንታኔ ጽሁፍን እና ቪዲዮን እያዘጋጀ ለሚመለከታቸው ሁሉ ያደርሳል። ከዚህም በተጨማሪ ወቅታዊ እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጥናታዊ ጽሁፎችን ያቀርባል።