ከ50ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አንድ የትዊተር ገፅ ወደ አማራ ክልል የሚሄዱ ወታደሮችን የጫነ አውሮፕላንን ያሳያል በማለት  አንድን ምስል አጋርቷል

ይህ ጽሁፍ እስከሚታተምበት ጊዜ ድረስ ፖስቱ​​​​ 61 ጊዜ ያህል ተጋርቶ እና ከ80 በላይ ግብረመልሶችን አግኝቶ ነበር።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ወደ አማራ ክልል የሚሄዱ ወታደሮችን የጫነ አውሮፕላንን እንደማያሳይ አረጋግጧል። በዚህም የትዊተር ፖስቱ ሀሰት ተብሏል።

እ.አ.አ በየካቲት 2023 የኢትዮጵያ መንግስት  የክልል ልዩ ሀይሎችን እንዲበተኑ እና ወደ መከላከያ ሰራዊት፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ወደ ክልል መደበኛ ፖሊስ እንዲቀላቀሉ ወስኗል። ይህም በአማራ ክልል የሚገኘውን ፋኖ በመባል የሚጠራውን የታጠቀ ቡድን  ያበሳጨና ተቃውሞ ያስነሳ ነው ። ይህን ተከትሎ በፋኖ ታጣቂዎችና  በመንግስት ወታደሮች መካከል ብዙ ግጭቶች ተካሂደዋል።

እ.ኤ.አ. ነሀሴ 11 ቀን 2023 የወጡ ዘገባዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎች እንዳመላከቱት በዚህ ግጭት ሳቢያ በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል።

ምንም እንኳን መንግስት የአማራ ክልል ትላልቅ ከተሞችን መልሶ ቢቆጣጠርም አሁንም በኢትዮጵያ ሰራዊት እና በፋኖ ሚሊሻ ቡድኖች መካከል ያለው ግጭት ቀጥሏል።

በዚህ መነሻነት የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በአውሮፕላን ወደ አማራ ክልል እያጓጓዘ እና እያሰማራ እንደሆነ የሚገልጽ አንድ የኤክስ (ትዊተር) ፖስት ተመልክተናል። ፖስቱ አንድ ምስል አያይዞ ነበር የተጋራው። ይህ በኤክስ የተጋራው ምስል  የመከላክያ ወታደሮች በሄሊኮፕተር ወደ አማራ ክልል እየተወሰዱ ያሳያል በማለት የቀረበ ነው።

ይሁን እንጂ ምስሉ ከቆየ ቪድዮ ላይ ተቆርጦ የተወሰደና ዋናው ምስል በፌስቡክ ነሀሴ 2 ቀን 2021 በተሰራጨ ቪዲዮ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወታደሮች፣ ሎጅስቲክስ እና የጦር መሳሪያን ወደ ትግራይ አጓጉዟል ከሚል ፖስት ላይ የተወሰደ ነው።

ስለዚህ ሀቅቼክ  የኤክስ ፖስቱን ሀሰት ብሎታል።

Similar Posts