በጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ ከ6ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ “በአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ቤቶች እየተቃጠሉ ነው።” በማለት አንድ ቪድዮን አጋርቶ ነበር።


ከዚህ በተጨማሪም ይህ የፌስቡክ ገፅ በአካባቢው ያሉ የታጠቁ ሚሊሽያዎች የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ንብረት እየዘረፉ እና እየገደሉ ነው በማለት መረጃን አጋርቷል።  
 

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ይህ የፌስቡክ ገፅ በቪድዮው ውስጥ የተጠቀመው ምስል የቆየ እንደሆነ እና መረጃውን እንደማይደግፍ አረጋግጦ ሀሰት ብሎታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በአጎራባች የኦሮሞ ልዩ ዞን በሆኑ አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭቶች በተደጋጋሚ እየተፈጠሩ ይገኛሉ።  

እንደ አንድ አንድ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ከሆነ ከሰሞኑ በነዚህ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተዋል።  

በጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች በአማራ ክልል ታጣቂዎች አማካኝነት የተቀናጀ ጥቃት በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ተፈፅሟል በማለት ገልጿል።   

ከዚህ በተጨማሪም በመግለጫው ላይ የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች እና የአካባቢው ሚሊሽያዎች በጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ፤ ቤቶችን እንዳቃጠሉ እና ንብረቶችን እንደዘረፉ ገልጿል። 

ከዚህ በተጨማሪም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በግጭቱ ከ65 በላይ ንጹሀን መሞታቸውን በመግለጫው ላይ አንስቷል።  

ይህ የፌስቡክ ፖስትም የሚቃጠሉ ቤቶችን የሚያሳይ የምስል ቪድዮ ያጋራው በዚህ ሀሳብ ላይ መሰረት አድርጎ ነው።


ይሁን እንጂ ከቪድዮው ማየት እንደሚቻለው ምስሎችን ገጣጥሞ በመጠቀም የተፈጠረ ነው።     

ነገር ግን በቪድዮው ውስጥ ያለው ምስል ከዚህ በፊት በታኅሣሥ 14 ቀን  2013 ዓ.ም ከተጋራ ፅሁፍ ላይ የተወሰደ ነው።  

ሊንክከዚህ ፅሁፍ ጋር የተጋራው ምስል በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን የሚኖሩ ብዙ ንፁሃን እንደተገደሉ በሚያሳይ ሪፖርት ስር ተጋርቷል።

ሀቅቼክ በዚህ የፌስቡክ ገፅ አማካኛነት መረጃውን ለመደገፍ የተጋራው ምስል የቆየ እና ከዚህ መረጃ ጋር የማይገናኝ መሆኑ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል። 

Similar Posts