በቅርቡ በፌስቡክ ላይ የወጣ አንድ ልጥፍ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ መሳብ የቻለ ሲሆን ይህም መንግስት ከ18 አመት በላይ ለሆኑ ዜጎች የታለመ የ35,000ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በምዝገባ ላይ ነው የሚል መረጃ ነው።ነገር ግን ይህ መረጃ ህብረተሰቡን ለማጭበርበር የተነደፈ ፈጠራ እንጂ እውነት አይደለም።

ሊንክ

በርካታ ግለሰቦች በአስተያየቶች መስጫ ክፍል ላይ ፍላጎታቸውን ሲገልጹ ነበር። በዚህ በፌስቡክ ላይ በተጋራው መረጃ ሰዎች የግል መረጃቸውን ማለትም ስም እና የባንክ አካውንት ቁጥሮችን እንዲመዘግቡ ሲደረግ ተመልክተናል።
ለመመዝገቢያ በማለትም የተመለከተው ድረ-ገፅ ሊንክ የማይሰራ ሆኖ አግኝተነዋል።

ሊንክ

የመንግስት ኤጀንሲዎች ለየትኛውም አይነት አገልግሎት ምዝገባ የግል መረጃ በሚፈልጉበት ግዜ በዘፈቀደ በግለሰብ በተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች ላይ ሳይሆን ጉዳዩ በሚመለከተው መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የሚድያ አውታር እንዲሁም በህጋዊ መደበኛ የሚድያ ተቋማት ብቻ ማስታወቂያዎችን ያሰራጫሉ። 

እንደዚህ አይነት ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ ልጥፎች ለአጭበርባሪዎች ሰፊ የማጭበርበሪያ መንገድን ይሰጣል። ለምሳሌ በዚህ ልጥፍ ስር ባለው የአስተያየት መስጫ ክፍል ላይ የመጀመሪያው ሰው አስተያየት በመጀመሪያ 1000ብር ማስገባት እንዳለባቸው ከዚያም ገንዘቡ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚለቀቅላቸው እና ይህንን መስፈርት የሚቀበሉ ሰዎች በውስጥ የመልዕክት መስመሩ (inbox) እንዲገናኙ ይጋብዛል። ይህ መልዕክት ይኑር እንጂ በዚህ መንገድ ሰዎች 1000ብር አስገብተው ቃል የተገባውን ገንዘብ ከአንድ ወር በኋላ አያገኙም።

ሊንክ

እንደዚህ አይነት ማጭበርበሮች እና የማጭበርበሪያ ድርጊቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተስፋፉ መጥተዋል። በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች ገንዘብ ንብረቶቻቸውን አጥተዋል። እነዚህ አጭበርባሪዎች ግለሰቦቹን የግል እና የፋይናንስ መረጃዎችን እንዲገልጹ ለማታለል እንደ ኢሜይል ፣ ሀሰተኛ ድረ-ገጾች ፣ ሀሰተኛ ማገናኛዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች ያሉ ቴክኒኮችን ይጠቀማሉ።

ብዙ ሰዎች በተጭበረበሩ የመገናኛ ዘዴዎች ምክንያት አሳማኝ ባህሪ ምክንያት የእነዚህ ማጭበርበሮች ሰለባ ይሆናሉ። የኦንላይን ላይ ማጭበርበሮች ፣ አጭበርባሪዎች ማንነታቸው ሳይታወቅ ድርጊቶችን የማከናወን ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ እና በይነመረቡ በሚሰጠው ሰፊ ተደራሽነት አማካኝነት እጅግ እየተስፋፋ መጥቷል። 

እየጨመረ የመጣውን ስጋት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት እና የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲናገሩ ይታያሉ። እነዚህ ተቋማት በኦንላይን ላይ የግል መረጃን አለማጋራት፣ የጥያቄዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እና አጠራጣሪ ድርጊቶችን ወዲያውኑ ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻሉ።

ሊንክ    

ሊንክ

እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም ፣ የአጭበርባሪዎች መበራከት እና በሚጠቀሟቸው የተለያዩ አጓጊ ስልቶች ህብረተሰቡን አሁንም ድረስ በማታለል ላይ ይገኛሉ። ለዚህም የተሻሻሉ እና ተደራሽ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ማህበረሰቡን በደንብ ማስተማር ያስፈልጋል። ከዚህም በተጨማሪ ህዝቡ እነዚህን መሰል ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያረጋግጡበትን መንገዶች ማሳወቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 

Similar Posts